Previous Page
page
Next Page
Copyright ©  2014 Solomon Hailu W.M.
All rights reserved.
 
Back to top
FAQs
የመፍቻ ገበታ (Keyboard) አስመልክቶ ምን ድጋፍ (Support) አለ፧
ሁሉም የኢትዮ ሀሁ ፊደሎች በለመዱትና ባለዎት መፍቻ ገበታ (Keyboard) ይሠራሉ።
ችግር ካለ ከፊደሎቹ ጋር የሚላክልዎትን ጠቃሚ ጽሁፍ ያንብቡ።
ፊደሎቹ ለማከንታሽ ይሆናሉ ወይ፧
አዎ ይሆናሉ። Unicode በተደገፉ በሁሉም መሳ፟ሊያ (Operating systems Mac, Pc etc) ይሠራሉ።
ፊደሎቹ ለሞባይል ስልኮች ይሆናሉ ወይ፧
ለነገሩ የኢትዮ ሀሁ ፊደሎች በዩኒኮድ በተደገፉ በማንኛውም መኪናዎች ( Devices ) ላይ ይሠራሉ።
ይሁንና የፊደሎች አገልግሎት በሞባይል ስልኮችን ለጊዜው የለም ለወደፊት ግን ይኖራል።
ኮምፕዩተር ለሌለው የኢትዮጵያ ህዝብስ ምን ተሠራ፧
ኢትዮጵያ ሀሁ የኒታ የፊደል ገበታ በሁሉም የኢትዮጵያ ቁንቋዎች ለህትመት የተዘጋጁ ፊደሎች ናቸው።
ፊደሎቹ የተቀረጹት፦
፨ በቀላሉ ለመማርና ለማስተማር ፣
፨ በጥቂት ነጥቦች ስለተሠሩ የእጅ ጽሁፍን በአጭር ጊዜ ለመማር ወይም ለማስተማር፣
፨ በሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ፊደሎች ስለሆኑ በተለይም ህጻናት በአጭር ጊዜ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ያግዛል።
በበለጠ ለመረዳት ስለ About ገጽ ላይ የሚገኘውን ኢትዮ ሀሁ ለምን ያንብቡ።
፨ ማስታወሻ፦ ፊደሎቹን ለማዳረስ አጋር ስለሚያስፈልግ፣ አብሮ ለመሥራት የምትፈልጉ ሁሉ ኢሜል ላኩልኝ።
ፈቃዱ እንዴት ነው የሚሰራው ፧
ፊደሎቹን ሲሸምቱ በተመዘገቡበት email አድራሻ ብቻ ነው።
ፈቃዱ ለስንት ዓመት ነው ፧
ለግለ ሰብ ለእድሜ ልክ።
ፈቃዱ ለግለ ሰብ ለስንት ኮምፕዩተሮች ነው፧
ለአንድ ኮምፕዩተር።
ልዩ ፈቃድ የሚያስፈልጋችው ምንምን ናቸው፧
መሥሪያ ቤቶችና በቡድን መጠቀም የሚፈልጉ የመሳስሉት ናችው።
ኮምፕዩተር ብቀይርስ፧ የ Backup ጉዳይስ፧
ፊደሎቹ የሚታዘዙት በሸማቹ email አድራሻና በ original license code ስለሆነ ችግር እይኖርም። ።
የመገልገያው ፍቃድ ቢጠፋብኝስ፧ አንዴት ነው የአዕምሮ እረፍት መግዛት የምችለው፧
የኢትዮ ሀሁ ፊደል ገበያ (Order)ገጽ ላይ ሁለት ምርጫዎች አሉ።
አንደኛው extended download service ሲሆን አገልግሎቱ original license code በአደራ ማስቀመጥ ሲሆነ ፤
ለዚህ አገልግሎት በዓምት $3.50 ከከፈሉ ያለ ሀሳብ ደጋግመው Download ማድረግ ያስችልዎታል።
ሁለተኛው ደግሞ በመላው ዓለም ( ከ ኩባ ፤ ኢራን ፤ ሲሪያ ፤ ሰሜን ኮርያ ፤ ሱዳንና ሊቢያ በስተቀር )
በመረጡት አድራሻ ለአሜሪካ ነዋሪዎች ፦ በ 7 ቀን ። ለ አውሮፓ ነዋሪዎ ፦ በ 14 ቀን ። በዓለም ዙሪያ ፦ በ 21 ቀን ።Backup CD ይላክልዎታል።
ፈቃዱን በስጦታ መልክ ለሌላ ሰው መግዛት ይቻላል ወይ፧
አዎ። ስጦታውን በደረቁ በEmail ብቻ ፤ ወይም ክ Online File Backup Protection ጋር ፥
ወይም ከ Backup CD ጋር መስጠት ይቻላል። ይህንን ለማድረግ ፦
መጀመሪያ ለስጦታ ፊደል ለመምረጥ Buy Nowን ቀጭ ማድረግ ፤
ቀጥሎየ፦ ኢትዮ ሀሁ ፊደል ገበያ (Order) ገጽ ላይ Order nowን ይጫኑ
በመጨረሻም የሚጨምሩትን ጨምረው የማይፈልጉትን ቀንሰው የስጦታ ተረካቢውን አድራሻ መሙላት ነው።
ፊደሎቹን መከራየት ይቻላል ወይ፧
አዎ። እንዱ የፊደል ዓይነት ለምሳሌ፦ ኢትዮ ሀሁ ክብ። በቀን ስሙኒ በወር ከነምናምኑ በድምሩ $10. ብቻ መከራየት ይቻላል።
ከመረጡት ፊደል ጎን የሚከራይን ቀጭ ያድርጉ ።
፠ማስታወሻ፦ የፊደሎቹ የኪራይ ዘመን ከማለቁ በፊት፦
ማስታወሻ ኢሜል ይላክልዎታል።
ኪራዩን መቀጠል ካልፈለጉ በኢትዮ ሀሁ የተሥሩ ሥራዎችዎን እንዳሉ ለመጠበቅ ወይም ፋይል ለማድረግ፦
፩ ኛው ዘዴ ወደ pdf ወይም ወደሚመችዎ Image format (አቀጻጽ) መቀየር አይዘንጉ!!!!
፪ ተኛው ዘዴ ማተም ነው።
፨ የኪራይ ዚዜ ገደብ ካለቀ በኋላ በተመሳሳይ ፊደል እርማት ለማድረግ እንዲጠቅምዎ በፈለጉት የፊደል ዐይነት Save ማድረግና አንድ ቀን
ማረም ቢፈልጉ ፦ መጀመሪያ ፊደሎቹን በማድመቅ ወይም በመምረጥ ቀጥሎ የኢትዮ ሀሁ ፊደል በመምረጥ መቀየር ይቻላል ።
፨ ማንኛውም የኢትዮጵያ ፊደሎች ወደ ኢትዮ ሀሁ ፊደሎች ለመቀየር መጀመሪያ ፊደሎቹን በማድመቅ ወይም በመምረጥ ቀጥሎ የኢትዮ ሀሁ ፊደል በመምረጥ መቀየር ይቻላል ።

ፈቃዱን በስጦታ ለድርጅት ወይም ለትምህርት ቤቶች መግዛት ይቻላል ወይ፧
አዎ ። በቅድሚያ Email ይላኩልኝ።
ማንኛውም ዓይነት የኢትዮጵያ ፊደሎች ወደ ኢትዮ ሀሁ ፊደሎች መቀየር ይቻላል ወይ፧
አዎ ይቻላል።ማንኛውም ዓይነት የኢትዮጵያ ፊደሎች ወደ ኢትዮ ሀሁ ፊደሎች ወይም የኢትዮ ሀሁ ፊደሎችን ወደ
ማንኛውም ዓይነት የኢትዮጵያ ፊደሎች ለመቀየር መጀመሪያ ፊደሎቹን በማድመቅ ቀጥሎ የሚፈልጉትን ፊደል
በመምረጥ መቀየር ይቻላል።
ፊደል አልፈልግም ግን አይዞህ ለማለት ፣ ለመደገፍ እፈልጋለሁ
ፊደል አልፈልግም ማገዝ ግን ግን እፈልጋለሁ የሚለውን ምስል ቀጭ ያድርጉ። ምስሉ በየገጾቹ ግርጌ ይገኛል።
በበለጠ ለመረዳት ስለ About ገጽ ላይ የሚገኘውን ጽሁፍ ያንብቡ።
አጋር Affiliate በመሆን ትርፍ ለመጋራት የሚቻለው እንዴት ነው ፧
ከድረ ገጹ በስተ ግርጌ ትርፍ የጋራን ቀጭ ያድርጉ ።
ኢትዮ ሀሁ ማከፋፈል እፈልጋለሁ ፣ ለነጋዴዎች ልዩ ዋጋ አለ ወይ ፧
በሚገባ። በተለይ አትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ነጋዴዎች ልይ ቅናሽ አለ። በበለጠ ለመረዳት ኢሜል ላኩልኝ።
የፈቃድና የማራባት ጉዳይ ስምምነት ለማንበብ እዚችጋ ጠቅ ያድርጉ።
Contact
ስለ ኢትዮ ሀሁ ለማን ፧ ለምን ፧ ወዴት ፧ ለማንበብ እዚችጋ ጠቅ ያድርጉ።
ሰለ
Ethiopian Font Foundry is Home of Ethiohahu.com
Fonts
የኢትዮጵያ ፊደል ቀረጻ ማዕከል ።